ቀጥታ፡

ወጣቶች በሥራ ላይ የሚያተኩሩ፤ሀገራቸውን ለማወቅ የሚተጉ፣ የሀገራቸውን ጸጋ የሚያለሙ፣ፈጣሪያቸውን አመስጋኝ መሆን አለባቸው-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

ነሐሴ 15 ቀን 2014 (ኢዜአ)ወጣቶች በሥራ ላይ የሚያተኩሩ፤ሀገራቸውን ለማወቅ የሚተጉ፣ የሀገራቸውን ጸጋ የሚያለሙ፣ፈጣሪያቸውን አመስጋኝ መሆን አለባቸው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።

ሀገራቸው ኢትዮጵያን በኅብረ ብሔራዊ አንድነት ማጽናት የዚህች ድንቅ ሀገር ልጆች ግዴታ ነው ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ጠቁመዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከመላው አገሪቱ ከተወጣጡ ወጣቶች ጋር በዛሬው እለት ውይይት እያካሄዱ ነው።

ውይይቱ መሰረታዊ የሆኑ የወጣቶችን ጥያቄዎች በተቀናጀ መንገድ ለመመለስ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ያለመ ሲሆን፤ ወጣቶች በአገር፣ በሰላም፣ በልማትና በዴሞክራሲ ግንባታ ሚናቸውን እንዲወጡ ለማስቻል የወጣቶች ሚና ወሳኝ መሆኑ ውይይት ይደረጋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም