በድሬደዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ ኤል አውቶ የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ ተመርቆ ስራ ጀመረ - ኢዜአ አማርኛ
በድሬደዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ ኤል አውቶ የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ ተመርቆ ስራ ጀመረ
ነሐሴ 14 ቀን 2014(ኢዜአ) ከድሬደዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሁለት ሼዶች ወስዶ የቅደመ ዝግጅት ስራ ሲያከናውን የቆየው ኤል አውቶ የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ በዛሬ ዕለት ተመርቆ ስራ ጀመረ።
ፋብሪካውን መርቀው ስራ ያስጀመሩት የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር ፣ የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽንዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሰንዶካን ደበበና የፋብሪካው ባለቤቶች እንዲሁም የፌደራል ከፍተኛ ባለስልጣናት ናቸው።
ፋብሪካው ከሁለት መቶ በላይ የሰለጠኑ ወጣቶች የስራ ዕድል መፍጠሩና በሶስት ፈረቃ ሰላሳ መኪናዎችን እንደሚገጣጥም ታውቋል።
የሚገጣጠሙ መኪናዎች የአገር ውስጥ የመኪና ፍላጎት ለማሟላት እና የውጭ ምንዛሬ ለማስቀረት እንደሚያስችል በምረቃው ላይ ተገልጿል ።
የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ በጎረቤት አገራትም ቅርንጫፍ በመክፈት ላይ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት እና የቴክኖሎጂ ዕውቀት ሽግግር በማድረግ የድርሻውን ለማበርከት እንደሚሰራ ነው የተገለፀው።