የጤና ሚኒስቴር ለ100 ሺህ ዜጎች ነጻ የሕክምና አገልግሎት ሊሰጥ ነው

122

ነሐሴ 13 ቀን 2014 (ኢዜአ) የጤና ሚኒስቴር 100ሺህ ለሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ነጻ የጤና ምርመራና የሕክምና አገልግሎት ለመስጠት መዘጋጀቱን አስታወቀ።

አገልግሎቱ "በጎነት ለጤናችን " በሚል መሪ ቃል ከነሀሴ 16 እስከ 21 ቀን 2014 ዓ.ም በኢትዮጵያ የተለያዩ ክፍሎች በበጎ ፈቃደኛ የጤና ባለሙያዎች እንደሚሰጥ ገልጿል።

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አገልግሎቱን አስመልክቶ በሚኒስቴሩ ቅጥር ግቢ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

ለስድስት ተከታታይ ቀናት በሚቆየው የበጎ ፈቃድ ስራ አቅመ ደካማ ለሆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎችና ለጎዳና ተዳዳሪዎች የተለያዩ የሕክምና አገልግሎት እንደሚሰጣቸው ሚኒስትሯ ገልጸዋል ።

ከሚሰጡ የጤና ምርመራዎች ውስጥ የስኳር ህመም ፣የደም ግፊት፣ የአይን ሕመም ሕክምና እንዲሁም ሌሎች ተላላፊ እና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ይገኙበታል።

ተላላፊ እና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን አስመልክቶ ለሕብረተሰቡ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ እንደሚከናወንም ነው ዶክተር ሊያ የገለጹት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም