ቀጥታ፡

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 20 ነጥብ 94 ቢሊዮን ብር ከሃይል ሽያጭ ተገኝቷል-የኤሌክትሪክ አገልግሎት

ነሐሴ 12 ቀን 2014(ኢዜአ) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 20 ነጥብ 94 ቢሊዮን ብር ከሃይል ሽያጭ ማገኘቱን አስታወቀ ።

የአገልግሎቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሽፈራው ተሊላ እንዳሉት በተጠናቀቀው በ2014 በጀት ዓመት ከኃይል ሽያጭ 20 ነጥብ 94 ቢሊዮን ብር በመሰብሰብ የእቅዱን 88 በመቶ ማሳካት ተችሏል።

በበጀት አመቱ 367 ሺህ 466 ደምበኞችን የኤሌክትሪክ ሃይል ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልፀው 204 አዳዲስ ከተሞች እና መንደሮች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ እንዲሆኑ መደረጉንም አንስተዋል።

በ2015 በጀት ዓመት ደግሞ ከኤሌክትሪክ ሃይል ሽያጭ እና ከሌሎች ገቢዎች በአጠቃላይ 43 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ በእቅድ መያዙን ነው የተናገሩት።

በተመሳሳይ 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን አዳዲስ ደምበኞች የኤሌክትሪክ ሃይል ተጠቃሚ ለማድረግም እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም