በአዲስ አበባ ነገ በአንድ ጀምበር 4 ሚሊየን ችግኝ ይተከላል

107

ነሐሴ 11 ቀን 2014 (ኢዜአ) በነገው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ በአንድ ጀምበር አራት ሚሊየን ችግኝ የመትከል መርሐ ግብር እንደሚካሄድ ተገለጸ፡፡

አረንጓዴ አሻራ የማሳረፍ መርሐ ግብሩ በአዲስ አበባ ከተማ በ11ዱም ክፍለ ከተሞች ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል፡፡

በዕለቱም ወጣቶች፣ ተማሪዎች፣ የፀጥታ አካላት፣ የእምነት አባቶች፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ ባለሃብቶች፣ በጎ ፈቃደኞች እና ሁሉም የከተማዋ ነዋሪ በየክፍለ ከተማው ለችግኝ መትከያ በተዘጋጁ ቦታዎች ላይ ደማቅ አረንጓዴ አሻራውን እንዲያሳርፍ ጥሪ መቅረቡን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም