ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የኬንያ ፕሬዚዳንት ሆነው ለተመረጡት ዊሊያም ሩቶ የደስታ መግለጫ መልዕክት አስተላለፉ

135

ነሐሴ 09 ቀን 2014 (ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በኬንያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ላሸነፉት ዊሊያም ሩቶ የኬንያ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ሆነው በመመረጥዎ “እንኳን ደስ ያልዎት” ሲሉ የደስታ መግለጫ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ተመራጩ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ቀጣዩ ጊዜ መልካም የስራ ጊዜ እንዲሆንላቸው መልካም ምኞታቸውን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ “የጋራ በሆኑ የሁለትዮሽና የቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተቀራርበን እንሰራለን” ሲሉ በትዊተር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ገልጸዋል።

በኬንያ በተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዊሊያም ሩቶ 50 ነጥብ 49 ድምጽ በማግኘት የቅርብ ተፎካካሪያቸው የነበሩትን ራይላ ኦዲንጋ አሸንፈዋል።

ተፎካካሪያቸው ኦዲንጋ 48 ነጥብ 8 ድምጽ አግኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም