የሳርቤት - ጎፋ ማዞርያ - የፑሽኪን ጎተራ ማሳለጫ ዘመናዊ የመንገድ ፕሮጀክት ተመረቀ

425

ነሀሴ 9/2014 /ኢዜአ/ የአዲስ አበባ ከተማን የትራንስፖርትአገልግሎት ያሳልጣል የተባለው የሳርቤት - ጎፋ ማዞርያ - የፑሽኪን ጎተራ የመንገድ ፕሮጀክት ተመረቀ ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ፣ የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክ ሚኒስትር ዳግማዊት ሞገስ የሳርቤት - ጎፋ ማዞርያ - የፑሽኪን ጎተራ ማሳለጫ ዘመናዊ የመንገድ ፕሮጀክትን መርቀው ከፍተዋል።

በአይነቱ ልዩ የሆነው የሳርቤት - ጎፋ ማዞርያ - የፑሽኪን ጎተራ ማሳለጫ ዘመናዊ የመንገድ ፕሮጀክት የከተማዋን የትራንስፖርት መጨናነቅ ከመፍታት አልፎ ገጽታዋን ለመቀይርም ትልቅ አቅም አለው።

ይህ በዛሬው ዕለት የተመረቀው መንገድ አዲስ አበባ ከተማን ስሟንና አለም አቀፍ ደረጃዋን የሚመጥን ነውም ተብሏል።

በከተማዋ የመንገድ ታሪክ የመጀመሪያና ዘመኑ የደረሰበትን የመንገድ ስራ ጥበብ የታየበት ፕሮጀክት እንደሆነም ተገልጿል።

የከተማ አስተዳደሩ አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ ብሎም የከተማዋን የትራንስፖርት ችግሮች ለመቅረፍ ከሚያደርጋቸው ከፍተኛ ጥረቶች አካል እንደሆነም ተመልክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም