የኢትዮጵያን የገቢና የወጪ ንግድ በከፍተኛ ሁኔታ የሚያሳልጠው የድሬደዋ ነፃ የንግድ ቀጠና ተመረቀ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያን የገቢና የወጪ ንግድ በከፍተኛ ሁኔታ የሚያሳልጠው የድሬደዋ ነፃ የንግድ ቀጠና ተመረቀ
237
ነሐሴ 8 ቀን 2014 (ኢዜአ) የኢትዮጵያን የገቢና የወጪ ንግድ በከፍተኛ ሁኔታ የሚያሳልጠው የድሬደዋ ነፃ የንግድ ቀጠና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መርቀው ከፍተውታል።
የንግድ ቀጠናው ለጅቡቲ ወደብ በቅርብ እርቀት ላይ መገንኘቱ የሀገሪቱን የገቢ ና የወጪ ንግድን አንደሚያሳልጥ ተመልክቷል።
የድሬደዋ ነፃ የንግድ ቀጠና የምስራቁን የኢኮኖሚ ኮሪደር እንቅስቃሴ በማሳለጥና የስራ እድል በመፍጠር ጭምር ጠቀሜታው ዘርፈ ብዙ መሆኑ ተገልጿል።