በወጣት አትሌቶቻችን የተደገመው አኩሪ ድል የኢትዮጵያዊያን የአሸናፊነት ስነ-ልቦና ትዉልድ ተሻጋሪ እሴት መሆኑን ያሳያል

141

በወጣት አትሌቶቻችን የተደገመው አኩሪ ድል የኢትዮጵያዊያን የአሸናፊነት ስነ-ልቦና ትዉልድ ተሻጋሪ እሴት መሆኑን ያሳያል፡፡

በኮሎምቢያ ካሊ ከተማ በተካሄደዉ የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን ወክሎ የተሳተፈው የልዑካን ቡድን አኩሪ ድል በማስመዝገብ አዲስ አበባ ገብቷል፡፡

May be an image of 7 people, people standing and indoor

መላዉ ኢትዮጵያዊያን እንኳን ደስ አላችሁ፣ እንኳን ደስ አለን!!በኮሎምቢያ ካሊ ከተማ በተካሄደዉ የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ኢትዮጵያ በወጣት አትሌቶቿ ከዓለም ሶስተኛ፣ ከአፍሪካ ደግሞ 1ኛ በመሆን አጠናቃለች፡፡

በዉድድሩም በአዋቂ አትሌቶቻችን በ18ኛዉ የዓለም የትሌቲክስ ሻምፒዮና የተበሰረው የአሸናፊነት ገድል በወጣት ተተኪ አትሌቶቻችንም ተደግሟል፡፡

ድሉ የአሸናፊነት ስነ-ልቦና ትዉልድ ተሻጋሪ የኢትዮጵያዊያን መለያ እሴት ስለመሆኑ ትልቅ ማሳያ ነዉ፡፡

ድል ማድረግ ብሎም ኢትዮጵያን በዓለም መድረክ ከፍ ማድረግ የአትሌቶቻችን መታወቂያ ነው፡፡

በዚህ የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ወጣት አትሌቶቻችን በአንድ ሰዓት ውስጥ ብቻ 5 የወርቅ ሜዳሊያ አሸንፈው ዓለምን አስደምመዋል፡፡

በውድድሩ በአጠቃላይ 6 ወርቅ፤ 5 የብር እና 1 የነሀስ ሜዳሊያዎችን ሰብስበዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም እምብዛም ውጤት አምጥታባቸው በማታውቀው የ1 ሺህ 500 እና 800 ሜትር እንዲሁም የመሰናክል ውድድሮች ሳይቀር የወርቅ ሜዳሊያዎች ተገኝተዋል፡፡

ይህም ኢትዮጵያ ያላትን የአትሌቲክስ እምቅ አቅም ከማሳየት አልፎ የአትሌቶቻቸችን የአሸናፊነት ስነልቦና የላቀ እንደሆነ ያመለክታል፡፡

ወጣት አትሌቶቻችን ያስመዘገቡት ድል ኢትዮጵያ የአሸናፊዎች ሀገር መሆኗን ለዓለም ማህበረሰብ ያሳየ ነበር፡፡

ኢትዮጵያ የመቻል አቅሟ የት ድረስ እንደሆነ፤ ተተኪ ባለድል ትዉልድ ያላት ጠንካራ ሀገር መሆኗንም ይጠቁማል፡፡

ኢትዮጵያ በፈተና ውስጥም ሆና ስኬትን የምታስመዘግብ፣ የማትሰበር ሀገር መሆኗን ወጣት አትሌቶቻችን ለአለም አሳይተዋል፡፡

ኢትዮጵያ በቀላሉ የማትሸነፍ፤ ህብረብሔራዊ አንድነት በየዕለቱ የሚያፀናት እና የሚያንፃት ሀገር እንደሆነች በኮሎምቢያ ካሊ ከተማ በተግባር ታይቷል፡፡

ኢትዮጵያ በልጆቿ ህብረት እና ጥንካሬ የስኬት ጉዞዋን አጠናክራ ትቀጥላለች፡፡

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም