በጋምቤላ ክልል የማስ ስፖርት መርሃ ግብር ተጀመረ

54

ነሐሴ 07 ቀን 2014 (ኢዜአ) በጋምቤላ ክልል የማስ ስፖርት መርሃ ግብር ዛሬ ተጀምሯል።

በጋምቤላ ከተማ በተጀመረው መርሃ ግብር የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እና የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።

ስፖርት ለሰላም፣ ለጤናና ለሕዝቦች አንድነት ያለውን ፋይዳ በማሰብ የተጀመረው የማስ ስፖርት መርሃ ግብሩ በየሳምንቱ እንደሚካሄድ ተነግሯል።

May be an image of 10 people, people standing and outdoors

በብልጽግና ፓርቲ የጋምቤላ ክልል ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ላክደር ላክባክ እንዳሉት፤ መርሃ ግብሩ በክልሉ ተቀዛቅዞ የነበረውን የስፖርት እንቅስቃሴ ለማጠናከር ያግዛል።

የክልሉ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ቱት ኮር በበኩላቸው መርሃ ግብሩ እንዲጀመር የተደረገበት አንዱ ምክንያት አመራሩን በዘርፉ በማሳተፍ ለክልሉ ስፖርት መጠናከር የአጋርነት ሚናውን ለማጠናከር በማሰብ እንደሆነም ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ፤

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም