የውሃ ሙሌቱ በስኬት መጠናቀቅ ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሀብቷ በመጠቀም የዜጎቿን የማደግ እና ከድህነት የመውጣት ተስፋ የሚያለመልም ነው

82

ነሃሴ 6 ቀን 2014/ኢዜአ/የውሃ ሙሌቱ በስኬት መጠናቀቅ ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሀብቷ በመጠቀም የዜጎቿን የማደግ፤ከድህነትና ጭለማ የመውጣት ተስፋ የሚያለመልም ነው ሲሉ የፍቼ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡

የህዳሴ ግድብ የሶስተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት መጠናቀቅ ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሀብቷ በመጠቀም መጪውን ጊዜ ብሩህና ተሰፋ ሰጪ የማድረግ አቅም እንዳላት አመላካች መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

የከተማው የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በህዳሴ ግድብ የሶስተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት መጠናቀቅ የተሰማቸውን ደስታ ዛሬ በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል፡፡

አስተያየት ሰጪዎቹ ኢትዮጵያ የውጪ ሀይሎችን ያልተገባ ጫና በመቋቋም ግድቡን ለሶስተኛ ዙር የውሃ ሙሌት ማብቃቷ እጅግ የሚያስደስትና የሚያኮራ ነው ብለዋል፡፡

ይኸም ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሀብቷ በመጠቀም የዜጎችን የማደግ፣ከድህነትና ጭለማ የመውጣት ተስፋ የሚያለመልም ነው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሀብቷ ያለማንም ከልካይ ከመጠቀም ባሻገር የጋራ ተጠቃሚነት ላይ ያላትን ፍትሃዊ አቋም ለአለም ህዝብ ያሳየችበት ነው ያሉት፡፡

ግድቡ ለፍፃሜ እስኪበቃ ቦንድ በመግዛት ችግኞችን በመትከልና በአካባቢያቸው ያሉ ተፋሰሶችን ከደለል ለመጠበቅ እንደሚሰሩም ጠቁመዋል፡፡

ግድቡ የኢትዮጵያ ህዝቦች በአንድነትና በትብብር ምን መስራት እንደሚችሉ ያመለከተ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

በቀጣይም ለግድቡ ግንባታ ቦንድ ከመግዛት ጀምሮ ህብረተሰቡን በማነቃቃት እንደሚሳተፉም ተናግረዋል፡፡

የውሃ ሙሌቱ ውስጣዊና ውጫዊ ጫናን በመቋቋም የኢትዮጵያውያንን አንድነትና በይቻላል መንፈስ ሰርቶ ማሳየትን በተግባር ያሳየ ነው ያሉት አስተያየት ሰጪዎች፡፡

ይኸም በራስ አቅም ተማምኖ ስራ መጀመርንና መጨረስ እንደሚቻል የሚያሳይ መሆኑን ገልጸው ፤የግድቡ የውሃ ሙሌት እና ሁለተኛው ተርባይን ሃይል ማመንጨት መጀመር ኢትዮጰያውያን በጉጉት ለሚጠብቁት የኤሌትሪክ ሃይል አቅርቦት መሰረት መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም