የህዳሴ ግድብ ሶስተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት በመጠናቀቁ የክልሉ ህዝብና መንግስት ከፍተኛ ደስታ ተሰምቶታል- አቶ ኡሞድ ኡጁሉ

231

ጋምቤላ፣ ነሐሴ 6 ቀን 2014 (ኢዜአ) የታላቁ ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ሶስተኛ ዞር የውሃ ሙሌት በስኬት በመጠናቀቁ የክልሉ ህዝብና መንግስት ደስታ የተሰማው መሆኑን የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ገለጹ።

ርዕሰ መስተዳድሩ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።ርዕሰ መስተዳድር ለኢዜአ እንደገለጹት የታላቁ ህዳሴ ግዳብ ሶስተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት የተጠናቀቀው የኢትዮጵያ ህዝብ አንድነቱን በማጠናከሩና ውስብስብ ፈተናዎች መሻገር በመቻሉ ነው።

ኢትዮጵያዊያን አንድነታችንን በማጠናከር ከሰራን የማንሻገረው ፈተና እና የማናስመዘግበው ድል እንደማይኖር ማሳያ ነው ብለዋል።

በቀጣይም ይህንን በማጠናከር የኢትዮጵያን ከፍታና ዕድገት ለማፋጠን መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በአንድነት ሊረባረብ እንደሚገባ ገልጸዋል።

የክልሉ ህዝብና መንግስት የግድቡ ግንባታ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ የተቻለውን ሁሉ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሰው፤ በቀጣይም የግድቡ ግንባታ እስኪጠናቀቅ የተጀመረው ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም