በአፋር ክልል በጦርነት የወደሙ የትምህርት ተቋማትን ለማስገንባት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ

57

ነሐሴ 6 ቀን 2014 (ኢዜአ) የትምህርት ሚኒስቴር በአፋር ክልል ጭፍራ ወረዳ በጦርነት የወደሙ የትምህርት ተቋማትን ለማስገንባት የመሰረት ድንጋይ አስቀመጠ።

የመሰረት ድንጋይ ያስቀመጡት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ኢለማ አቡበከር ናቸዉ።

ትምህርት ቤቱ ሜንሺን ፎር ሜንሺን በተባለ ግብረ ሰናይ ድርጂት የገንዘብ ወጪ የሚሰራ ነዉ።

በስነ-ሰርአቱ ላይ የወረዳዉ አመራሮች የሀገር ሽማግሌዎችና ሃይማኖት አባቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸዉና አካሎች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም