የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛው የኃይል ማመንጫ ዩኒት ኃይል ማመንጨት መጀመሩ የኢትዮጵያ ህዝብ የመደጋገፍና አንድነት ውጤት ነው - ዶክተር ይልቃል ከፋለ - ኢዜአ አማርኛ
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛው የኃይል ማመንጫ ዩኒት ኃይል ማመንጨት መጀመሩ የኢትዮጵያ ህዝብ የመደጋገፍና አንድነት ውጤት ነው - ዶክተር ይልቃል ከፋለ
ነሐሴ 05 ቀን 2014 (ኢዜአ) የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛው የኃይል ማመንጫ ዩኒት ኃይል ማመንጨት መጀመሩ የኢትዮጵያ ህዝብ የመደጋገፍና አንድነት ውጤት ነው ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ ገለጹ።
በአንድነት ከቆምን ለስኬት እንደምንበቃ ማረጋገጫ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ እንኳን ደስ አለን ሲሉ የመልካም ምኞት መግለጫ አስተላልፈዋል።
ከሁሉም በላይ የጋራ ጠላት የሆነውን ድህነት ማሸነፍ የምንችለው ያለንን የተፈጥሮ ፀጋ በጋራ አልምተን በአግባቡ መጠቀም ስንችል መሆኑን መረዳት ይገባል ብለዋል።
ከተባበርንና ከተደጋገፍን ዳር የማናደርሰው የልማት ተግባር የለም፤ ለዚህ ደግሞ ታላቁ የህዳሴ ግድብ አንዱ ማሳያ ነው ሲሉም ገልጸዋል።
ግድቡ እውን እንዲሆን በተደረገው ሁለንተናዊ ተሳትፎ የበኩላቸውን ለተወጡ ኢትዮጵያውያን እንኳን ደስ አላችሁ፤ እንኳን ደስ አለን ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመልክቷል።