ቀጥታ፡

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ተርባይን ሃይል ማመንጨት ማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት እየተካሄደ ነው

ነሃሴ 5/2014/ኢዜአ/ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ተርባይን ሃይል ማመንጨት ማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት እየተካሄደ ነው፡፡

በስነ-ሰርዓቱ ላይ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ዛሬ ሃይል ማመንጨት የሚጀምረው ዩኒት ዘጠኝ ሲሆን፥ 270 ሜጋ ዋት ሃይል የማመንጨት አቅም እንዳለው ተጠቁሟል።

የታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ካሉት 13 የኃይል ማመንጫ ተርባይኖች መካከል የመጀመሪያው ተርባይን የካቲት 13 ቀን 2014 ዓ.ም ኃይል ማመንጨት መጀመሩ ይታወሳል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ፤

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም