ሕጋዊ ሰነድ ሳይኖራቸው በኢትዮጵያ የሚገኙ የውጭ ዜጎች ምዝገባ መራዘሙን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ - ኢዜአ አማርኛ
ሕጋዊ ሰነድ ሳይኖራቸው በኢትዮጵያ የሚገኙ የውጭ ዜጎች ምዝገባ መራዘሙን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ
ነሃሴ 5/2014/ኢዜአ/ ሕጋዊ ሰነድ ሳይኖራቸው በኢትዮጵያ የሚገኙ የውጭ ዜጎች ምዝገባ እስከ ነሐሴ 13 ቀን 2014 ዓ.ም መራዘሙን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የሚኒስቴሩ ቃል-አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ የኢትዮጵያ መንግሥት የውጭ ዜጎችን ሕጋዊ የማድረግ ምዝገባ እስከ ነሐሴ 13 ተራዝሟል ብለዋል።
እስካሁን በተደረገው ምዝገባ ከ70 ሺህ በላይ የሚሆኑ የ36 አገራት ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች ተመዝግበዋል።
ምዝገባው የተራዘመው በመጀመሪያ ዕድል ያልተመዘገቡ ሌላ ዕድል እንዲያገኙ በማሰብ ነው ብለዋል።
ቃል-አቀባዩ በመግለጫቸው በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠረው ችግር በሰላም እንዲፈታ አሁንም ፅኑ አቋም መኖሩን አንስተዋል።
ችግሩን ለመፍታት የሰላም አማራጩ የሚካሄደው በአፍሪካ ሕብረት በኩል ብቻ እንደሆነና ሌላ አካል ተቀባይነት እንደሌለው አሁንም ፅኑ ፍላጎት አለ ብለዋል።
ከሰሞኑ በአፍሪካ ሕብረት የሰላም ኮሚሽን ወጣ የተባለ ሐሰተኛ መረጃ እንጂ ሕጋዊ ሰነድ እንዳልሆነ ገልጸዋል።
በአፍሪካ ጉዳይ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡን ከአፍሪካ ሕብረት ጋር አቻ አድርጎ ማንሳትም ቅቡልነት እንደሌለው ገልጸዋል።
መንግሥት በትግራይ ክልል መሰረታዊ አገልግሎት ማስጀመር ለሰላም አማራጩ እንደ ቅድመ-ሁኔታ አይወስድም ብለዋል።