ሀገር ዓቀፉ ከወለድ ነፃ የፋይናንስ እና ኢኮኖሚ ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
ሀገር ዓቀፉ ከወለድ ነፃ የፋይናንስ እና ኢኮኖሚ ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው
ነሃሴ 5/2014/ኢዜአ/ ሀገር ዓቀፋ ከወለድ ነፃ የፋይናንስ አገልግሎት እና ኢኮኖሚ ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
በኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት የተሰናዳው ጉባኤ "አካታች የፋይናንስ አገልግሎት በኢትዮጵያ ውስጥ ተደራሽ ማድረግ" በሚል መሪ ሐሳብ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
ጉባኤውም ከወለድ ነፃ የፋይናንስ አገልግሎት ስርዓትን በተሻለ መልኩ ተደራሽ ለማድረግ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ተገልጿል።
በኢትዮጵያ ከወለድ ነፃ የፋይናንስ አገልግሎት ያለው እድልና እጣፋንታ፣ የሸሪዓ አስተዳደርና ከወለድ ነፃ የፋይናንስ አገልግሎት የአሰራር ስርዓት በኢትዮጵያ በሚል ርዕስ ጉዳይ ምክክር እንደሚደረግ ይጠበቃል።
በተጨማሪም የዲጂታል ቴክኖሎጂ የፋይናንስ ስርዓትና ከወለድ ነፃ የፋይናንስ አገልግሎት የአሰራር የሚሉት ርዕሰ ጉዳዮች በጉባኤው ምክክር ይደረግባቸዋል።
በጉባኤው ላይ የፋይናንስ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ፤ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሀመድ ኢድሪስ፤ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ፣ ጨምሮ ሌሎች የኃይማኖት አባቶች፣ የመንግስት እና የፋይናንስ ተቋማት ኃላፊዎች እና የዲያስፖራ አባላት ተገኝተዋል።