የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ጉባኤ የተለያዩ አዋጆችና ሹመቶችን በማጽደቅ ተጠናቀቀ

219

ሚዛን አማን፣ ነሐሴ 05 ቀን 2014 (ኢዜአ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ለሁለት ቀናት ሲያካሂድ የቆየውን 6ኛ ዙር 1ኛ የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ የክልሉን ብዝሃ ከተሞችና ሌሎች አዋጆችንና ሹመቶች በማፅደቅ ትናንት ማምሻውን ተጠናቋል።

ምክር ቤቱ የቀረቡለትን 5 የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።

በተመሳሳይ ለክልሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 8 ዳኞችን እንዲሁም ለተለያዩ ወረዳ እና ከተማ አስተዳደሮች የቀረቡ 22 እጩ ዳኞችን ሹመት ተቀብሎ አጽድቋል።

May be an image of 10 people

የተሾሙ ዳኞች በፌዴራል ዳኞች አስተያየት የተሰጠባቸውና የትምህርት ዝግጅት፣ የማኅደር ጥራትና ሥነ ምግባርን መስፈርት በማድረግ የታጩ መሆናቸው ተገልጾ፤ በምክር ቤቱ ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ፤

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም