የሥራና ክሂሎት ሚኒስቴር በሚያስደንቅ ሁኔታ ራሱን አዋቅሮ ሥራና ክሂሎትን የመፍጠር ተልዕኮውን በብቃት መከወን ጀምሯል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

160

ሐምሌ 30 ቀን 2014 (ኢዜአ) በቅርቡ የተቋቋመ ተቋም እንደ መሆኑ፣ የሥራና ክሂሎት ሚኒስቴር በ10 ወራት ውስጥ ብቻ በሚያስደንቅ ሁኔታ ራሱን አዋቅሮ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ሥራና ክሂሎትን የመፍጠር ተልዕኮውን በብቃት መከወን ጀምሯል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ።

የሥራ ዕድልን ማመቻቸት ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህንኑ የሚያሳልጥ በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የተቋቋመው የሥራ ዕድል ፈጠራ ተግዳሮቶችን በብቃት ለመወጣት እንዲሁም የሠለጠነ የሰው ኃይልና የአገልጋይነት አመለካከት ያላቸውን አገልጋዮችን ለማብቃት እንዲቻል ነው ብለዋል።

የሥራ ዕድል ፈጠራን በበቂ ሁኔታ ለማመቻቸት፣ መሥሪያ ቤቱ ያለው ብቃት ሊጠናከርና ሊፋጠን ያስፈልጋል ሲሉም በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ገልጸዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ፤

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም