ቀጥታ፡

ኮርፖሬሽኑ በ'አርዳይታ' ምርጥ ዘር እርሻ ልማት አካባቢ ለሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች የ 5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

ሀምሌ 30/2014/ኢዜአ/ የኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን በ'አርዳይታ' ምርጥ ዘር እርሻ ልማት አካባቢ ለሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ለትምህርት ቤት ማስፋፊያና ኤሌክትሪክ ሀይል ማስገቢያ የሚውል 5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

ድጋፉም በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን 'አርዳይታ' ምርጥ ዘር እርሻ ልማት አጎራባች ለሚገኘው የ'ወልተኢ' ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማስፋፊያ እና ለ'ወልተኢ' ቀበሌ ኤሌክትሪክ ማስገቢያ የሚውል ነው ተብሏል።

ድጋፉን የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ክፍሌ ወልደማርያም እና ሌሎች የስራ ሃላፊዎች ለአከባቢው የአገር ሽማግሌዎችና ተወካዮች አስረክበዋል።

የአከባቢው ነዋሪዎችም ለተደረገላቸው ድጋፍ አመስግነው ኮርፖሬሽኑ የጀመረውን ስራ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

ኮርፖሬሽኑ ከዚህ ቀደምም በአርሲ ዞን አሰላ ከተማ፣ በምዕራብ አርሲ ዞን ኮፈሌ ከተማና በአርዳይታ ምርጥ ዘር እርሻ ልማት አካባቢ የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያድርጉ የውሃ፣ የጤና እና የትምህርት ተቋማትን ማስገባቱም ተገልጿል።

በተያያዘም የኮርፖሬሽኑ አመራሮችና ሰራተኞች በአርዳይታ ምርጥ ዘር እርሻ ልማት ግቢ ውስጥ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አከናውነዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም