ቀጥታ፡

አምባሳደር ባጫ ደበሌ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ አቀረቡ

ሐምሌ 30 ቀን 2014 (ኢዜአ) በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው የተሾሙት አምባሳደር ባጫ ደበሌ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለአገሪቱ ፕሬዚዳንት አሁሩ ኬንያታ አቅርበዋል።

አምባሳደር ባጫ በኢትዮጵያ እና ኬንያ መካከል ረዥም ዓመታት ያስቆጠረውን እንዲሁም ባለ ብዙ ዘርፍ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ይበልጥ ለማጎልበት እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

May be an image of 2 people, people standing and indoor

አምባሳደር ባጫ በኬንያ የተሾሙ 16ኛው የኢትዮጵያ አምባሳደር መሆናቸውን በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያ እና ኬንያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን የጀመሩት እ.አ.አ በ1961 መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ፤

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም