ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ከአክሱም ዩኒቨርሲቲ በአደራ የተቀበላቸውን ተማሪዎች ጨምሮ ከ300 በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ - ኢዜአ አማርኛ
ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ከአክሱም ዩኒቨርሲቲ በአደራ የተቀበላቸውን ተማሪዎች ጨምሮ ከ300 በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ
ሆሳዕና፣ ሐምሌ 30 ቀን 2014 (ኢዜአ) የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ከአክሱም ዩኒቨርሲቲ በአደራ የተቀበላቸውን 34 ተማሪዎች ጨምሮ በህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅና በተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት ክፍሎች ያሰለጠናቸውን 321 በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ።
ዩኒቨርሲቲው ለ11ኛ ዙር በህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በህክምና፣ በህክምና ጤና ሳይንስ የትምህርት ዘርፎችና በባዮቴክኖሎጂ የትምህርት ክፍሎች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ናቸው የተመረቁት።
ከተመራቂ ተማሪዎቹ ዉስጥ 44ቱ በህክምና ዶክተሬት፤ 243 በህክምና ጤና ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ በመጀመሪያ ድግሪ የሰለጠኑ እንደሆነ ተገልጿል።
ቀሪ 34ቱ ደግሞ ከአክሱም ዩኒቨርሲቲ በአደራ በመቀበል በተፈጥሮ ቀመር ሳይንስ የትምርህርት ዘርፍ በባዮቴኖሎጂ ትምህርት ክፍል ያሰለጠናቸው ተማሪዎች ናቸው።
በተማሪዎቹ የምረቃ ስነ-ስርዓት ላይ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር ዶክተር አለሙ ስሜ፣ የኢትዮጵያ ፕሮፌሰሮች ማህበር አባልና የዩኒቨርሲቲው የስራ አመራር ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ፕሮፌሰር ጀማ ሀጂን ጨምሮ የተለያዩ እንግዶች፣ የተመራቂ ተማሪዎችና ቤተሰቦችና የአካባቢው ማህበረሰብ አባላት ተገኝተዋል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ፤