የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቋርጦት የነበረውን ወደ ማኒላ ከተማ በረራ በድጋሚ ጀመረ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቋርጦት የነበረውን ወደ ማኒላ ከተማ በረራ በድጋሚ ጀመረ
ሐምሌ 29 ቀን 2014 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት አቋርጦት የነበረውን ወደ ማኒላ ከተማ በረራ በድጋሚ መጀመሩን አስታወቀ።
በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት የተጣሉ ገደቦች በመነሳታቸው ምክንያት አየር መንገዱ ወደ ማኒላ በሳምንት ሶስት ጊዜ የሚያደርገውን በረራ መቀጠሉን አመልክቷል።
በተያያዘ ዜና አየር መንገዱ ከጥቅምት 20 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ስዊዘርላንድ ዙሪክ በረራ እንደሚጀምር ያስታወቀ ሲሆን ይህም ዓለም አቀፍ መዳረሻዎቹን ወደ 129 እንደሚሳድጋቸው ጠቁሟል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ሰኔ 25 ቀን 2014 ዓ.ም ወደ ሕንድ ቼናይ በረራ መጀመሩ ይታወሳል።
በተጨማሪም በግሪክ አቴንስ፣ በሳውዲ አረቢያ ደምማን፣ በኢንዶኔዥያ ጃካርታ እና በባህሬን አዳዲስ በረራዎችን እንደሚጀምር መግለጹ ይታወቃል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ፤