ቀጥታ፡

የመከላከያ ኃይል ስምሪት ኃላፊና ጊዜያዊ የፀጥታ ኮማንድፖስት አስተባባሪ ሜጀር ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው በቀጠናዊ ሰላምና ጸጥታ ዙሪያ ከሶማሊያ የአስተዳደርና ጸጥታ አካላት ጋር ተወያዩ

ሐምሌ 28 ቀን 2014 (ኢዜአ) የመከላከያ ኃይል ስምሪት ኃላፊና ጊዜያዊ የፀጥታ ኮማንድፖስት አስተባባሪ ሜጀር ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው በቀጠናዊ ሰላምና ጸጥታ ሁኔታ ላይ ከሶማሊያ የአስተዳደርና ጸጥታ አካላት ጋር ውይይት አደረጉ።

ሜጀር ጄኔራሉን ጨምሮ ከፍተኛ የመከላከያ ሰራዊት አመራሮች እና የጸጥታ አካላት ያካተተ ቡድን በደቡብ ምዕራብ ሶማሊያ ባይድዋ ከተማ በነበረው ቆይታ የአልሻባብ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ እንዲሁም ቀጠናዊ ሰላምና ጸጥታን አስመልክቶ በሴክተሩ ዋና አዛዥ ገለጻ እንደተደረገለት የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት አስታውቋል።

May be an image of 10 people, people standing and outdoors

ቡድኑ ከደቡብ ምዕራብ ሶማልያ መስተዳድርና የጸጥታ አካላት ጋር ስለ ቀጠናው ሰላምና የጸጥታ ሁኔታ በተለይም አልሸባብን ለመደምሰስ በሚካሄደው ዘመቻ በቅንጅት መስራት ስለሚቻልበት ሁኔታ መወያየቱ ገልጿል።

ከቀናት በፊት የመከላከያ ሚኒስቴር የመረጃ ደህንነት ኃላፊ ሌተናል ጀኔራል ብርሃኑ በቀለ በቀጠናው ሊኖር ስለሚገባው የጋራ የጸጥታና ደህንነት ጉዳዮች ትብብር አስመልክቶ ከሶማሌላንድ የመንግስት ባለስልጣናትና የጸጥታ ኃላፊዎች ጋር መወያየታቸው ይታወሳል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ፤

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም