በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጭ ዘመናዊ ሎጅ ሊገነባ ነው

196

ሐምሌ 27 ቀን 2014 (ኢዜአ)በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን ደራ ወረዳ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጭ የዋንዛየ ዘመናዊ ሎጂ ሊገነባ መሆኑ ተገለጸ።

ዘመናዊ ሎጁን የአማራ ልማት ማህበር (አልማ) የሚያስገነባው ሲሆን የመሰረት ድንጋይም ዛሬ ተቀምጧል።

የአልማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መላኩ ፋንታ በስነ ስርዓቱ ላይ እንዳሉት አልማ የክልሉን ህዝብ የልማት ጥያቄ ለመመለስ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል።

ማህበሩ እያከናወናቸው ከሚገኙት የጤና፣የትምህርትና የሌሎች ልማት ስራዎች በተጨማሪ ለገቢ ማስገኛ ዘርፉ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ነድፎ እያከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።

ከገቢ ማስገኛ ፕሮጀክቶች መካከልም ከአንድ ቢሊዮን በላይ በሆነ ወጭ የሚያስገነባው የዋንዛየ ዘመናዊ ሎጂ ግንባታ አንዱ መሆኑን ገልፀዋል።

ፕሮጀክቱን በሁለት ዓመታት ውስጥ ገንብቶ ለአገልግሎት ለማብቃት የአማራ ህንፃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት የኩንትራት ውል መውሰዱን ገልፀዋል።

በደራ ወረዳ ዋንዛየ ፍል ውሃ የሚገነባው ዘመናዊ ሎጂ ሲጠናቀቅ 155 የተለያየ ደረጃ ያላቸው የምኝታ አልጋዎች፣ሁለት የመሰብሰቢያ አዳራሾች፣ሦስት ሬስቶራንቶች፣ሁለት የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎችና ሁለት የፍል ውሃ መዋኛ ገንዳዎችንና ሌሎችም ያካተተ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም