ኢትዮጵያ እና ባህሬን በኢንቨስትመንትና ቱሪዝም ዘርፍ ያላቸውን ግንኙነት ለማጠናከር እየተሰራ ነው - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ እና ባህሬን በኢንቨስትመንትና ቱሪዝም ዘርፍ ያላቸውን ግንኙነት ለማጠናከር እየተሰራ ነው
ሐምሌ 26 ቀን 2014 (ኢዜአ)ኢትዮጵያ እና ባህሬን በኢንቨስትመንትና ቱሪዝም ዘርፍ ያላቸውን ግንኙነት ለማጠናከር እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ።
በባህሬን የኢትዮጵያ ቆንስል ጄኔራል አምባሳደር አወል ወግሪስ መሀመድ በባህሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሮ-ኤስያ ጉዳዮች ዋና ኃላፊ አምባሳደር ፋጢማ አብዱላ አዛዒን ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም ሁለቱን ሀገራት ሊያቀራርቡና ሊያስተሳስሩ የሚችሉ ጉዳዮች ተግባራዊ እንዲሆኑ መክረዋል።
በባህሬን የሚኖሩ ዜጎች መብታቸው ስለሚከበርበት ሁኔታ፣በሁለቱ ሀገራት መካከል የኢንቨስትመንትና ቱሪዝም ፍሰትን ለማጠናከር ስለሚቻልበት አግባብ ዙሪያ መክረዋል።
የባህሬን ቱሪስቶችና ባለሃብቶች ከኢትዮጵያ አቻዎቻቸው ጋር ተገናኝተው የሚወያዩበት ሁኔታ ስለሚመቻችበት አግባብ ላይ መወያየታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።