ቀጥታ፡

መንግስት ወደ ትግራይ ክልል አስፈላጊው ሰብአዊ ድጋፍ ተደራሽ እንዲሆን በቁርጠኝነት እየሰራ ነው

ሐምሌ 26 ቀን 2014 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ መንግስት ወደ ትግራይ ክልል አስፈላጊው የሰብአዊ ድጋፍ ተደራሽ እንዲሆን በማድረግ ረገድ በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑ ተመላከተ፡፡

በጂቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋየ በጅቡቲ አዲስ ከተሾሙት የአልጄሪያ አምባሳደር ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከአልጄሪያ ጋር የላትን ግንኙነት ከፍተኛ ትኩረት እንደምትሰጥ አምባሳደር ብርሃኑ በዚህ ወቅት ተናግረዋል።

ሁለቱ አገራት አልጄሪያ በ1962 ነፃ ከመውጣቷ በፊት ፀረ ቅኝ ግዛት ትግል በጋራ ማድረጋቸውን አንስተው፤ ግንኙነታቸው በሁለትዮሽ እና በባለብዙ ወገን ስትራቴጂካዊ ትብብር እንዳላቸውም አክለዋል።

አምባሳደሩ አክለውም ለአልጄሪያ አቻቸው የኢትዮጵያ መንግስት ሁሉም አስፈላጊ ሰብአዊ ድጋፎች ትግራይ ክልል መድረሳቸውን በማረጋገጥ ላይ ስላደረገው የማያወላውል ቁርጠኝነት አብራርተዋል።

አምባሳደሮቹ በሌሎች ቀጠናዊና አህጉራዊና አለማቀፋዊ ጉዳዮችም ላይ መክረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም