የጤና ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በልደታ ከፍለ ከተማ አስጀመሩ

157

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25 ቀን 2014 (ኢዜአ) የጤና ሚኒስቴርና በስሩ የሚገኙ ተጠሪ ተቋማት የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በልደታ ከፍለ ከተማ ዛሬ አስጀምረዋል።

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ መርሐግብሩን በክፍለ ከተማው ወረዳ 5 የአቅመ ደካሞች የቤት ግንባታ እድሳት አስጀምረውታል።

ጤና ሚኒስቴርና በስሩ የሚገኙ 12 ተጠሪ ተቋማት በዘንድሮው መርሐግብር የ12 አቅመ ደካሞችን ቤት እንደሚገነቡ ተገልጿል።

በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሐግብሩ ላይ ሚኒስትር ዴኤታዎችና የተጠሪ ተቋማት ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በ2013 ዓ.ም መርሐግብር የጤና ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ የ22አቅመ ደካሞችን ቤት ገንብተዉ ማስረከባቸው ተነግሯል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም