የኢትዮጵያ መድን ድርጅት አመራርና ሰራተኞች የአረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት አመራርና ሰራተኞች የአረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ
ሐምሌ 23 ቀን 2014(ኢዜአ) የኢትዮጵያ መድን ድርጅት አመራርና ሰራተኞች የአረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ።
የድርጅቱ አመራርና ሰራተኞች 4ኛውን ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በማስመልከት በአዲስ አበባ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አያት አካባቢ ችግኝ ተክለዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የተሳተፉት የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ነፃነት ለሜሳ፤ ችግኞችን በመትከልና በመንከባከብ ለአረንጓዴ ልማታችን ስኬት የድርሻችንን እየተወጣን ነው ብለዋል።
በዛሬው መርሃ ግብር 10 ሺህ ችግኞች መተከላቸውን ጠቅሰው ቀጣይም ችግኞችን መትከልና መንከባከባችን ይቀጥላል ብለዋል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ