ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ሰራተኞችና አመራሮች የአረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ

ሐምሌ 23 ቀን 2014(ኢዜአ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ሰራተኞችና አመራሮች ዛሬ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 አካባቢ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ አካሄደዋል።

አየር መንገዱ በዘንድሮው መርሐግብር ከ100 ሺህ በላይ ችግኞችን ለመትከል እቅድ መያዙ ተገልጿል።

May be an image of 3 people and outdoors

የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር "ዐሻራችን ለትውልዳችን" በሚል መሪ ሃሳብ 6 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ በመሰራት ላይ ይገኛል።

በአገር አቀፍ ደረጃ እስካሁን 5 ቢሊዮን ችግኞችን መትከል እንደተቻለም ከመርሃ ግብሩ አስተባባሪ ኮሚቴ ለማወቅ ተችሏል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም