ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰራተኞች የአረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ

ሐምሌ 23 ቀን 2014 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰራተኞችና ማኔጅመንት አባላት በአዲስ አበባ ለሚኩራ ክፍለ ከተማ የአረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ።

የባንኩ ሰራተኞችና የማኔጅመንት አባላት 4ኛውን ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በማስመልከት ችግኝ ተክለዋል።

በመርሐግብሩ ላይ የባንኩን ፕሬዝደንት አቤ ሳኖ ጨምሮ ሌሎችም የተገኙ ሲሆን ችግኝ ከመትከላቸው ቀደም ብለው በ"ኢትዮጵያ ታመስግን" ጥሪ መሰረት የምስጋና ስነ ስርአት አከናውነዋል።

በመቀጠልም የባንኩ ሰራተኞችና የማኔጅመንት አባላቱ በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ፀሐይ ሪል እስቴት ተብሎ በሚጠራው ችግኞቸን ተክለዋል።

የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር "ዐሻራችን ለትውልዳችን" በሚል መሪ ሃሳብ እየተከናወነ ሲሆን በአገር አቀፍ ደረጃ እስካሁን 5 ቢሊዮች ችግኞች መተከላቸው ታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም