ኢትዮጵያ ለኬንያ ዋነኛ የኤሌክትሪክ ሀይል አቅራቢ ሃገር ሆናለች - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ ለኬንያ ዋነኛ የኤሌክትሪክ ሀይል አቅራቢ ሃገር ሆናለች
ሐምሌ 22 ቀን 2014(ኢዜአ)የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ለኬንያ ዋነኛ የኤሌክትሪክ ሀይል አቅራቢ መሆኑን የኬንያ የኤሌክትሪክ ሀይል አስታወቀ፡፡
ኢትዮጵያ ለኬንያ የኤሌክትሪክ ሀይል ለማቅረብ ሰሞኑን ስምምነት መፈረሟን ተከትሎ በኤሌክትሪክ ሀይል አቅርቦት በሁለተኛነት እንደምትቀመጥ ተገልጿል፡፡
አሁን ላይ ለኬንያ ከፍተኛውን የኤሌክትሪክ ሀይል እያቀረበ የሚገኘው ኬን ጄን ሀይድሮ ኢስተርን የተሰኘ ድርጅት ነው፡፡
ኢትዮጵያ በቅርቡ ከኬንያ ጋር በተፈራረመችው ስምምነት መሰረት አንድ ኪሎ ዋት በሰዓት ከ6 እስከ 7 የኬንያ ሽልንግ ሳንቲም ለማቅረብ ውል መፈጸማቸውን የኬንያ የሀይል አስተዳደር ዳይሬክተር ኢንጂነር ጂዎፍሬይ ሙሊ ጠቁመዋል፡፡
ስምምነቱ ኢትዮጵያ አሁን ላይ 200 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ለኬንያ ለመሸጥ የሚያስችላት ሲሆን በቀጣይ ደግሞ ኢትዮጵያ ለኬንያ የምታቀርበውን የኤሌክትሪክ ኃይል መጠን እስከ 400 ሜጋ ዋት ከፍ ለማድረግ ያለመ ነው፡፡
የውል ስምምነቱን በኢትዮጵያ በኩል የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር እዮብ ተካልኝ በኬንያ በኩል ደግሞ ፕሬዚደንት ኡሁሩ ኬንያታ በኬንያ መፈራረማቸው ይታወሳል፡፡