"ኢትዮጵያ ታመስግን" የምስጋና መርሐግብር በታላቁ አንዋር መስጅድ ተካሄደ - ኢዜአ አማርኛ
"ኢትዮጵያ ታመስግን" የምስጋና መርሐግብር በታላቁ አንዋር መስጅድ ተካሄደ
ሐምሌ 22 2014 (ኢዜአ) "ኢትዮጵያ ታመስግን" የምስጋና መርሐግብር በታላቁ አንዋር መስጅድ ዛሬ ተካሄዷል ።
መርሐግብሩ የተካሄደው የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የጁመዓ ሰላትን ተከትሎ የምስጋና መርሐግብሩ እንዲደረግ ባስታወቀው መሰረት ነው ተብሏል።
የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በዚሁ ቀን በመላው ኢትዮጵያ ያሉ የእስልምና እምነት ተከታዮች ከጁመዓህ ስግደት በኋላ የሶስት ደቂቃ የምስጋና ጸሎት እንዲደረግ ጥሪ ማስተለፉም ይታወቃል።
በመርሐግብሩ ላይ ለሀገር ፣ለሰላም፣ ለመሪዎች እንዲሁም ለኢትዮጵያ ዱአ(ፀሎት እና ልመና) ተደርጓል።
በጉባኤው ጥሪ መሰረት ነገ የአድቬንቲስት እምነት ተከታዮች እንዲሁም ከነገ በስቲያ የኦርቶዶክስ ፣የካቶሊክ የፕሮቴስታንት የእምነት ተቋማት ከቅዳሴና መርሐግብሮቻቸው በኋላ ለፈጣሪ ምስጋና እንደሚያቀርቡ ተገልጿል።