በአርኪዮሎጂ ሥፍራዎችና በፓርኮች የሚከናወኑ የአረንጓዴ አሻራ ተግባራት አካባቢዎቹን በመጠበቅ በረሃማነት እንዳይስፋፋ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው-አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ - ኢዜአ አማርኛ
በአርኪዮሎጂ ሥፍራዎችና በፓርኮች የሚከናወኑ የአረንጓዴ አሻራ ተግባራት አካባቢዎቹን በመጠበቅ በረሃማነት እንዳይስፋፋ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው-አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ
ሐምሌ 22 ቀን 2014(ኢዜአ) በአርኪዮሎጂ ሥፍራዎች እና በፓርኮች ላይ የሚከናወነው የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር አካባቢው አንዲጠበቅና በረሃማነት እንዳይስፋፋ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ተናገሩ፡፡
የኢትዮጵያ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ኃላፊዎችና ሠራተኞች ቀርሳ መሊማ ወረዳ በሚገኘው የአርኪዮሎጂ ሥፍራ በሆነው መልካ ቁንጥሬ "የአርኪዮሎጂ ሳይት" የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር አካሂደዋል።
በወረዳው ለሚገኙ ለአቅመ ደካማ ተማሪዎችም የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል።
የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ አረንጓዴ አሻራ ማኖር የፓርኮችን የደን ሽፋን ከፍ በማድረግ በውስጡ የሚገኙ የዱር እንስሳቶች እንዳይሰደዱ ያደርጋል ብለዋል።
እንዲሁም የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎች፣ የአየር ንብረት ሁኔታው ምቹ እና ሳቢ እንዲሆን በማድረግ የቱሪስቶችን ፍሰት ይጨምራል ነው ያሉት።
የአርኪዮሎጂ ሥፍራዎችን እና በፓርኮች በረሃማነት እንዳይስፋፋ በማድረግ ረገድ አስተዋጽኦው ከፍተኛ ነውም ብለዋል።
የኢትዮጵያ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው፤ የተተከሉ ችግኞች አላማ የቱሪስት መዳረሻዎችን ከአፈር መሸርሸር ለመጠበቅ እና አረንጓዴ እና ምቹ ለማድረግ ነው ብለዋል።