በኦሪገን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ባመጣነው ውጤት እየተደሰትን ለቀጣይ ውጤቶችም መዘጋጀት አለብን - ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ - ኢዜአ አማርኛ
በኦሪገን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ባመጣነው ውጤት እየተደሰትን ለቀጣይ ውጤቶችም መዘጋጀት አለብን - ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ
ሀምሌ 21/2014/ኢዜአ/ በኦሪገን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ባመጣነው ውጤት እየተደሰትን ለቀጣይ ውጤቶችም መዘጋጀት አለብን ስትል የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ገለጸች።
በድል ለተመለሰው የአትሌቲክስ ቡድንም ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ በተገኙበት በብሄራዊ ቤተ መንግስት አቀባበል በማድረግ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ መልእክት ያስተላለፈችው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ፤ በአዲስ አበባ ለተደረገው ደማቅ አቀባበል አመስግናለች።
ፕሬዝዳንቷ በንግግሯ "ሁሉንም ማመስገን እፈልጋለሁ፤ መንግስት ከየትኛውም ጊዜ በላይ በብዙ መልኩ አግዞናል" በማለት የላቀ ምስጋናዋን አቅርባለች።
ከዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ድል መልስ ለተደረገው ደማቅ አቀባበል በተለይም ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፤ በብዙ መልኩ ላደረጉት እገዛ የላቀ ምስጋና አቀርባለሁ ብላለች ኮማንደር ደራርቱ።
በአሜሪካ ኦሪገን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒቶና ባመጣነው ውጤት እየተደሰትን ለቀጣይ ውጤቶችም መዘጋጀት አለብን ስትል መልእክቷን አስተላልፋለች።
ለልኡካን ቡድኑ በብሄራዊ ቤተ መንግስት ደማቅ አቀባበል በማድረግ የልኡካን ቡድኑ አባላትና ስፖርተኞች ሽልማት ተበርከቶላቸዋል።