10 ሜዳሊያዎችን ለሃገሩ ላስገኘው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን በአዲስ አበባ ነዋሪዎች አቀባበልና ምስጋና ስነ ስርዓት እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
10 ሜዳሊያዎችን ለሃገሩ ላስገኘው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን በአዲስ አበባ ነዋሪዎች አቀባበልና ምስጋና ስነ ስርዓት እየተካሄደ ነው
ሀምሌ 21/2014/ኢዜአ/ በ18ኛው የዓለም አትሌትክስ ሻምፒዮና 10 ሜዳሊያዎችን ለሃገሩ ላስገኘው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን በአዲስ አበባ ነዋሪዎች አቀባበልና ምስጋና ስነ ስርዓት እየተካሄደ ነው፡፡
ትናንት ምሽት አዲስአበባ የገባው የአትሌቲክስ ልዑካን ቡድኑ ባረፈበት ስካይ ላይት ሆቴል በማርሽ ባንድ የታጀበ አቀባበልም ተደርጎለታል፡፡
በአቀባበሉ ላይ የልዑካን ቡድኑ ቤተሰቦች ፣ክለቦችና ፌደሬሽኖች ባረፈበት ስካይ ላይት ሆቴል የአበባ ጉንጉን አበርክተዋል፡፡
ቡድኑ ካረፈበት ስካይላይት ሆቴል ተነስቶ በእስጢፋኖስ ፣ 4 ኪሎ ፣ ፒያሳ ፣ ቸርችል አድርጎ በለገሀር ወደ መስቀል አደባባይ በመሄድ ደስታውን ከህዝብ ጋር እየገለፀ ይገኛል፡፡