ቀጥታ፡

የአትሌቶቻችን ድል ከግላዊ ይልቅ አገርን ማስቀደምና የኢትዮጵያ ከፍታ ላይ እንድንሰራ ያሳየ ነው- የሐረር ከተማ ነዋሪዎች

ሀረር፣ ሐምሌ 20 ቀን 2014 (ኢዜአ) የአትሌቶቻችን ድል ከግላዊ ይልቅ አገርን ማስቀደምና የኢትዮጵያ ከፍታ ላይ እንድንሰራ ያሳየ ነው ሲሉ የሐረር ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።

ነዋሪዎቹ ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት በአሜሪካን ኦሪገን የተካሄደው የአለም አትሌቲክስ ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ከግላዊ ድል ይልቅ አገራዊን በማስቀደም የኢትዮጵያን ከፍታ ያጎለበቱበትና ለሌላውም ምሳሌ የሆነ ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ከከተማው ነዋሪዎች መካከል አቶ እንዳልካቸው ማሞ እንደተናገሩት ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች አንድነትን አስቀድመው ባከናወኑት ድልና በተገኘው ወርቅና ብር እጅግ ተደስተዋል።

አትሌቶቹ በቡድን በመሆን ያከናወኑት ስራ ተተኪ አትሌቶችና ኢትዮጵያዊያን ከግላዊ ይልቅ የቡድንና አብሮነት ስራ ለተሻለ ውጤት እንደሚያበቃ በግልጽ ያሳዩበት ነው።

ድሉ የኢትዮጵያን ውድቀት ለሚሹ እና ሰላሟን የማይፈልጉ አካላትን ቅስም የሰበረ፣ የኢትዮጵያውያን ጀግንነት በዓለም አደባባይ የታየበትና ጠላቶቿ ያፈሩበት ነው ያለው ሌላው የከተማው ወጣት ዝነኛው ከዱ ነው።

በአትሌቶቹ የታየው ፍቅር፣መሰናሰልና አንድነትን በስፖርቱና ሁሉም መስክ ተጠናክሮ መቀጠልና ለአገር አለኝታ መቆም ይገባል ብሏል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም