ቀጥታ፡

የሃይማኖት አባቶች የአረንጓዴ አሻራ አካል የሆነ የሰላምና የአብሮነት አሻራ በሐዋሳ ከተማ ታቦር ተራራ ላይ አኖሩ

ሐምሌ 20 ቀን 2014 (ኢዜአ) የሃይማኖት አባቶች የአረንጓዴ አሻራ አካል የሆነ የሰላም እና የአብሮነት አሻራ በሐዋሳ ከተማ በሚገኘው ታቦር ተራራ ላይ አኖሩ።

የሐዋሳ ቅዱስ ገብርኤል ንግስ በዐል በሠላም መጠናቀቁን ምክንያት በማድረግ የከተማው አስተዳደር ባዘጋጀው የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር የሃይማኖት አባቶች አሻራቸውን አኑረዋል።

በመርሐግብሩ የሲዳማ ክልል የሃይማኖት ተቋማት አባቶች፣ የከተማው አስተዳደር ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ጸጋዬ ቱኬ፣ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተወሕዶ ቤተክርስትያን፣ የሲዳማ ቡርጂ፣ አማሮ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ዮሴፍ፣ የሲዳማ ክልል እስልምና ጉዳይ ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሀጂ ሙስጠፋ ናስር ተሳትፈዋል።

በዚህ ወቅት የሃማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉሃን ታጋይ ታደለ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የሀይማኖት አባቶች በሐዋሳ ከተማ ታቦር ተራራ ላይ በጋራ አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።

መርሐግብሩ የተከናወነው የአረንጓዴ አሻራ ተሳትፎ የሰላም እና የአብሮነት አሻራ በሚል መሪ ሃሳብ መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም