በሻምፒዮናው ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገበው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን በአሜሪካ የምስጋናና የእራት ግብዣ ተደረገለት - ኢዜአ አማርኛ
በሻምፒዮናው ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገበው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን በአሜሪካ የምስጋናና የእራት ግብዣ ተደረገለት
ሐምሌ 20 ቀን 2014(ኢዜአ)በ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገበው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን በአሜሪካ የምስጋናና የእራት ግብዣ ተደረገለት፡፡
ለአትሌቲክስ ቡድኑ ግብዣውን ያደረጉት በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ፣ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልእክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ፣በኒው ዮርክ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቢሮ እና የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አባላት በጋራ በመሆን ነው።
በአቀባበሉና በግብዣው ስነ ስርዓት ላይም የአትሌቲክስ ቡድኑ በኦሪገኑ 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ በመሳተፍ በታሪኩ ከፍተኛ የሆነውን ውጤት በማስመዝገቡ እንኳን ደስ አላችሁ ተብሏል፡፡
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን በሻምፒዮናው 4 ወርቅ፣4 ብር እና 2 ነሐስ በድምሩ 10 ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ በማምጣት ከአሜሪካ በመቀጠል ከዓለም 2ኛ በመውጣት ማጠናቀቁ ይታወሳል፡፡