የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ አዲስ አበባ ገቡ - ኢዜአ አማርኛ
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ አዲስ አበባ ገቡ
ሀምሌ 19 ቀን 2014 /ኢዜአ/ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ አዲስ አበባ ገቡ፡፡
በአፍሪካ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ አዲስ አበባ ገብተዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቦሌ አየር ማረፊያ ሲደርሱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ላቭሮቭ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ከኢትዮጵያ መንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ ተገልጿል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ በግብጽ፣ በኮንጎ ብራዛቪልና በኡጋንዳ ጉብኝት ማድረጋቸውም ታውቋል፡፡
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በ2018 በኢትዮጵያ ባደረጉት ጉብኝት ሁለቱ አገራት በኃይል ልማት፣ ባቡር ዝርጋታ፣በንግድና ኢንቨስትመንት ያላቸውን ትስስር ለማጠናከር የሚያስችሉ ስምምነቶችን መፈራረማቸው የሚታወስ ነው።