ቀጥታ፡

በ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን አቀባበል ይደረግላቸዋል

ሀምሌ 19/112014 /ኢዜአ/ በ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን አባላት ደማቅ አቀባበል ለማድረግ ዝግጅት መጠናቀቁን ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ገለጸ።

ኢትዮጵያ በአሜሪካ ኦሪገን በተካሄደው 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አራት ወርቅ፣ አራት ብርና ሁለት የንሐስ  ሜዳሊያዎችን አግኝታለች።

በውጤቱም ከአፍሪካ ቀዳሚ ስትሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከአሜሪካ ቀጥሎ ሁለተኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች።

ይህ ውጤት ያስመዘገቡ  አትሌቶችና ሌሎች የልዑካን ቡድን አባላት ደማቅ አቀባበል እንደሚደረግላቸው ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ገልጿል ።

የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጀላ መርዳሳ የአትሌቲክስ ቡድን አባላቱ ኢትዮጵያን ያኮራ ውጤት ማስመዝገባቸውን ገልጸዋል።

በዚህም ደማቅ አቀባበል ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን  ተናግረዋል ።

አትሌቶች ከፍተኛ ውጤት ከማምጣታቸው በተጨማሪ በቡድን ስራም ያሳዩት ተግባር የሚደነቅ መሆኑን ነው የተናገሩት ።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን አባላት ነገ ምሽት አዲስ አበባ የሚገቡ ሲሆን፤ ከነገ በስቲያ ሐሙስ በአዲስ አበባ በተመረጡ ቦታዎች ህዝቡ አቀባበል እንደሚያደርግላቸው ተናግረዋል፡፡

በዚህም የልዑካን ቡድኑ አባላት በስካይ ላይት ሆቴል አራት ኪሎ፣ ፒያሳ፣ ችርቸል ጎዳና እና መስቀል አደባባይ የሚንቀሳቀሱ ይሆናል፡፡

በብሔራዊ ቤተ መንግስት እውቅና ሽልማት እንደሚደረግላቸውም ነው ያነሱት፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም