አየር መንገዱ ወደ ዙሪክ በረራ ሊጀምር ነው - ኢዜአ አማርኛ
አየር መንገዱ ወደ ዙሪክ በረራ ሊጀምር ነው
ሐምሌ 19 ቀን 2014 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ወደ ስዊዘርላንድ ዙሪክ ጥቅምት 20 ቀን 2015 ዓ.ም በረራ እንደሚጀምር አስታወቀ።
ወደ ዙሪክ የሚጀምረው በረራ የአየር መንገዱን ዓለም አቀፍ መዳረሻ ወደ 129 እንደሚያሳድገው ገልጿል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ሰኔ 25 ቀን 2014 ዓ.ም ወደ ሕንድ ቼናይ በረራ መጀመሩ ይታወሳል።
በተጨማሪም በግሪክ አቴንስ፣ በሳውዲ አረቢያ ደምማን፣ በኢንዶኔዥያ ጃካርታ እና በባህሬን አዳዲስ በረራዎችን እንደሚጀምር መግለጹ ይታወቃል።