በአዲስ አበባ በኤሌክትሪክ ኃይል ተሸካሚ መስመር ላይ በሚኖር የማሻሻያ ስራ በተወሰኑ አካባቢዎች የኃይል መቋረጥ እንደሚኖር ተገለጸ - ኢዜአ አማርኛ
በአዲስ አበባ በኤሌክትሪክ ኃይል ተሸካሚ መስመር ላይ በሚኖር የማሻሻያ ስራ በተወሰኑ አካባቢዎች የኃይል መቋረጥ እንደሚኖር ተገለጸ

ሐምሌ 18 2014(ኢዜአ) በአዲስ አበባ ከተማ በኤሌክትሪክ ኃይል ተሸካሚ መስመር ላይ በሚኖር የማሻሻያ ስራ በተወሰኑ አካባቢዎች የኃይል መቋረጥ እንደሚኖር የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ።
በከተማዋ የኤሌክትሪክ ኃይል ተሸካሚ መስመር ላይ በሚደረግ የማሻሻያ ስራ ነገ እና ከነገ በስቲያ በተወሰኑ አካባቢዎች የኤሌትሪክ ኃይል መቋረጥ እንደሚኖር ነው የተገለጸው።
በዚሁ መሰረት ማክሰኞ ሐምሌ 19 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 2 ሰአት እስከ ቀኑ 9 ሰአት ድረስ በኬንያ ኤምባሲ፣ በእንግሊዝ ኤምባሲ፣ በእስራኤል ኤምባሲ እና አካባቢዎቻቸው የኃይል መቋረጥ ይኖራል ብሏል።
ረቡዕ ሐምሌ 20 ቀን 2014 ዓ.ም ደግሞ ከጠዋቱ 2 ሰአት እስከ ቀኑ 9 ሰአት ድረስ በጎሮ አለማየው ሕንጻ፣ በሮቤራ ኮፊ፣ በሜታ፣ በአትሌቲክስ ፌዴሬሽን፣ በጉርድ ሾላ፣ በአየር መንገድ ቤቶች እና አካባቢዎቻቸው፤በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 2 ሰአት ከ30 እስከ ቀኑ 11 ሰአት በአይካ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ፣ በአለም ገና ኢንዱስትሪ መንደር፣ በአለም ገና ማርስ ብስኩት፣ በጌጃ፣ በፉሪ፣በሃጂ ሪል አስቴት፣ በጀሞ 2 ኮንደሚኒየም፣ በየስ ውሃ እና አካባቢዎቻቸው ኤሌክትሪክ እንደሚቋረጥ አመልክቷል።
በተጠቀሱት አካባቢዎች የሚገኙ ደንበኞች ይህን በመገንዘብ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አሳስቧል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ