የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ያሰለጠናቸውን መኮንኖች አስመረቀ

14

ሐምሌ 17 ቀን 2014 (ኢዜአ)የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ያሰለጠናቸውን 104 ከፍተኛ እና መካከለኛ መኮንኖች አስመርቋል።

የምረቃ ስነስርዓት ላይ ተገኝተው ማዕረግ ያለበሱት እና የስራ መመሪያ የሰጡት የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር ናቸው።

በተጨማሪም የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፈቲያ አደን ጨምሮ ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ ወርሰሜ እና የካቢኔ አባላት በትምህርታቸው ከፍተኛ ውጤት ላመጡት መኮንኖች ሽልማቶችን አበርክተዋል።

በስነ ስርዓቱ ላይ የአገር ሽማግሌዎች፣ዑጋዞች፣አባገዳዎች እና ነዋሪዎች እና የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።

የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ከፍተኛ እና መካከለኛ የፖሊስ መኮንኖችን በራሱ አቅም አስተምሮ ሲያስመርቅ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም