የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መርሃ ግብሮች ያሰለጠናቸውን የፖሊስ መኮንኖችን እያስመረቀ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መርሃ ግብሮች ያሰለጠናቸውን የፖሊስ መኮንኖችን እያስመረቀ ነው
ሐምሌ 16 ቀን 2014 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በተገኙበት በተለያዩ መርሃ ግብሮች ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 631 የፖሊስ መኮንኖችን እያስመረቀ ነው።
በምርቃት መርሃ ግብሩ ላይ ፕሬዚዳንቷን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።
ዩኒቨርሲቲው በማስመረቅ ላይ የሚገኘው ሰልጣኞች በሁለተኛ ዲግሪ፣ በመጀመሪያ ዲግሪና በዲፕሎማ እንዲሁም በሰርተፍኬት ያሰለጠናቸውን ሲሆን ሰልጣኞቹም በፖሊሰ ሳይንስ፣ በስነ-ወንጀልና ወንጀል ፍትህ፣ በወንጀል ምርመራ እንዲሁም በፖሊስ መኮንንነት ዘርፍ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።
በተጨማሪም ከምረቃ መርሃ ግብሩ ጎን ለጎን ለከፍተኛ አመራሮች የማዕረግ እድገት እንደሚሰጥ ተነግሯል።የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ከተቋቋመ 75 ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን፥ በቅርቡም ከኮሌጅነት ወደ ዩኒቨርሲቲ ደረጃ ማደጉ ይታወሳል።