የመንገድ ዘርፉ የሚመራበትን ግልፅ አቅጣጫ የሚያስቀምጥ ፖሊሲ እየተዘጋጀ ነው-የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር

92

ሐምሌ 15 ቀን 2014 (ኢዜአ) የመንገድ ዘርፉ የሚመራበትን ግልፅ አቅጣጫ የሚያስቀምጥ ፖሊሲ እየተዘጋጀ መሆኑን የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

ሚኒስቴሩ ባዘጋጀው ረቂቅ የመንገድ ፖሊሲ እና አዋጅ ላይ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡

በዚሁ ወቅት የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ እንዳሉት እየተዘጋጀ ያለው ፖሊሲ ከመንገድ ዘርፍ ጋር ተያይዞ የሚነሱ ችግሮችን ይፈታል፡፡

በዘርፉ ያሉ ውስብስብ ችግሮች የመንገድ ጥያቄ፣የተፈጠረውን ኃብት በአግባቡ የመጠበቅ፣የአገር ውስጥ ስራ ተቋራጮች እና አማካሪዎች አቅም በሚፈለገው መልኩ ያለማደግ፣የወሰን ማስከበር ችግሮች፣የግበዓት ችግሮች እና ሌሎችንም ለመፍታት ፖሊሲው ያግዛል ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ የመንገድ ፖሊሲና አዋጅ ባለመኖሩ የመንገድ ዘርፉን በአግባቡ ለመጠቀም እና ለመምራት እንዳልተቻለ ገልፀዋል፡፡

በአገሪቱ የመንገድ አውታር በ1989 ዓ.ም ከነበረበት 26 ሺህ 500 ኪሎ ሜትር አሁን ከ160 ሺህ ኪሎ ሜትር መድረሱንም ጠቁመዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም