ዋልያዎቹ በቻን የእግር ኳስ ውድድር ከደቡብ ሱዳን ጋር የማጣሪያ ጨዋታውን ዛሬ ያደርጋል - ኢዜአ አማርኛ
ዋልያዎቹ በቻን የእግር ኳስ ውድድር ከደቡብ ሱዳን ጋር የማጣሪያ ጨዋታውን ዛሬ ያደርጋል
ሐምሌ 15 ቀን 2014 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን(ዋልያዎቹ) በአገር ውስጥ ሊግ የሚገኙ ተጫዋቾች ብቻ ለሚሳተፉበት የአፍሪካ እግር ኳስ ሻምፒዮና(ቻን) ከደቡብ ሱዳን ጋር የማጣሪያ ጨዋታውን ዛሬ ያደርጋል።
ሰባተኛው የቻን የእግር ኳስ ውድድር እ.አ.አ በ2023 በአልጄሪያ አስተናጋጅነት ይካሄዳል።
ዋልያዎቹ የውድድሩን የመጀመሪያ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ከቀኑ 10 ሰአት 60 ሺህ ተመልካች በሚያስተናግደው ቤንጃሚን ምካፓ ስታዲየም ከደቡብ ሱዳን አቻቸው ጋር ያደርጋሉ።
ብሔራዊ ቡድኑ ጨዋታው በሚደረግበት ስታዲየም ለሁለት ቀናት ልምምድ አድርጓል።
የማጣሪያው የመልስ ጨዋታ ሐምሌ 24 ቀን 2014 ዓ.ም ይከናወናል።
ዋልያዎቹ ደቡብ ሱዳንን በድምር ውጤት ካሸነፉ ወደ ውድድሩ ለማለፍ ከሩዋንዳ ብሔራዊ ቡድን ጋር የመጨረሻ የማጣሪያ ጨዋታቸውን እ.አ.አ 2022 ነሐሴ ላይ ያደርጋሉ።
ሰባተኛው የቻን የእግር ኳስ ውድድር እ.አ.አ 2023 ጥርና የካቲት ወራት በአልጄሪያ አስተናጋጅነት ይካሄዳል።
ውድድሩ እ.አ.አ ነሐሴ 2022 መካሄድ የነበረበት ቢሆንም በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምከንያት መራዘሙ የሚታወስ ነው።
የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የተሳታፊዎች ቁጥር በመጨመር ከዚህ ቀደም በሻምፒዮናው የሚሳተፉ 16 አገራትን በአልጄሪያው ውድድር ወደ 18 ከፍ ማድረጉ ይታወቃል።