ቀጥታ፡

አምባሳደር ሀሰን ኢብራሂም በግብጽ ቆይታቸው በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ጥንታዊ ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚሰሩ ተናገሩ

ሐምሌ 14 ቀን 2014 (ኢዜአ) በግብጽ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሀሰን ኢብራሂም በግብፅ ቆይታቸው በኢትዮጵያና ግብፅ መካከል ያለውን ጥንታዊ ግንኙነት ያገናዘበ የሁለትዮሽ ግንኙነት ትርጉም ባለው መልኩ እንዲጠናከር እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

አምባሳደር ሃሰን የሹመት ደብዳቤያቸውን ቅጅ ለግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕሮቶኮል ጉዳዮች ዋና ሃላፊ ነቢል ሀብሺ አቅርበዋል።

አምባሳደር ሀሰን ኢብራሂም በግብጽ ቆይታቸው ሚስዮኑ በሚሸፍናቸው አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልድ ኢትዮጵያውያን ያሉባቸውን ችግሮች ለመቅረፍ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

ለጊዜው ተቋርጠው የቆዩ የድጋፍ አገልግሎቶች በተሟላ ሁኔታ እንዲጀመሩ ልዩ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ እና ዜጎች በያሉበት ለሀገራቸው የሚያበረክቱትን በጎ አስተዋጽኦ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል።

የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕሮቶኮል ጉዳዮች ኃላፊ በበኩላቸው አምባሳደር ሃሰን ኢብራሂም የግብፅ የስራ ቆይታ ውጤታማ እንዲሆን መልካሙን እንደሚመኙላቸው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም