ቀጥታ፡

ዋልያዎቹ በቻን የእግር ኳስ ውድድር ከደቡብ ሱዳን ጋር ለሚያደርጉት ጨዋታ ወደ ታንዛንያ አመሩ

ሐምሌ 13 ቀን 2014 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) በአገር ውስጥ ሊግ የሚገኙ ተጫዋቾች ብቻ ለሚሳተፉበት የአፍሪካ እግር ኳስ ሻምፒዮና(ቻን) ከደቡብ ሱዳን ላለበት የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታአታንዛንያ ዳሬ ሰላም አምርቷል።

ሰባተኛው የቻን የእግር ኳስ ውድድር እ.አ.አ በ2023 በአልጄሪያ አስተናጋጅነት ይካሄዳል።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን(ዋልያዎቹ) የውድድሩን የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ከደቡብ ሱዳን አቻው ጋር በታንዛንያ ሐምሌ 15 እና 24 ቀን 2014 ዓ.ም ያካሄዳል።

በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ የሚመራው የዋልያዎቹ ስብስብ ለጨዋታው ከሐምሌ 6 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በአዳማ ዝግጅቱን ሲያደርግ ቆይቷል።

የመጨረሻ ልምምዱንም ትናንት አካሂዷል።ዋልያዎቹ ደቡብ ሱዳንን በድምር ውጤት ካሸነፉ ወደ ውድድሩ ለማለፍ ከሩዋንዳ ብሔራዊ ቡድን ጋር የመጨረሻ የማጣሪያ ጨዋታቸውን እ.አ.አ 2023 ነሐሴና መስከረም ወራት ያደርጋሉ።

ሰባተኛው የቻን የእግር ኳስ ውድድር እ.አ.አ ከጥር 13 እስከ የካቲት 4 2023 በአልጄሪያ አስተናጋጅነት ይካሄዳል።

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የተሳታፊዎች ቁጥር በመጨመር ከዚህ ቀደም በሻምፒዮናው የሚሳተፉ 16 አገራትን በአልጄሪያው ውድድር ወደ 18 ከፍ አድርጓል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም