ባለፉት 10 ሳምንታት ብቻ ከ130 ሺህ ቶን በላይ ምግብና ምግብ ነክ ድጋፍ ወደ ትግራይ ተልኳል - የዓለም ምግብ ፕሮግራም

23

ሐምሌ 12 ቀን 2014 (ኢዜአ) ባለፉት 10 ሳምንታት ብቻ ከ130 ሺህ ቶን በላይ ምግብና ሌሎች ሰብዓዊ ድጋፎች ወደ ትግራይ መላካቸውን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዓለም ፕሮግራም ገለጸ።

በዓለም ምግብ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ተወካይ ክላውድ ጂቢዳር እንደገለጹት፤ መንግስት የሰብዓዊ ድጋፍ ወደ ትግራይ ክልል እንዲገባ መፍቀዱን ተከትሎ የዓለም የምግብ ፕሮግራም የሚያቀርበውን ሰብዓዊ እርዳታ በከፍተኛ ሁኔታ አሳድጓል።

May be an image of train, sky and railway

በሌላ በኩልም የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በሰሜን ኢትዮጵያ በአማራ፣ ትግራይና አፋር ክልሎች ለሚገኙና በጦርነት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የሰብዓዊ እርዳታ የሚውል 60 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ማድረጉንም ተወካዩ ተናግረዋል።

ድጋፉ በጦርነት ምክንያት ከቀዬአቸው ለተፈናቀሉ፣ ለምግብ እጥረት ለተጋለጡ ህጻናት፣ እናቶች እና አቅመ-ደካሞች ለአደጋ ጊዜ የምግብ አቅርቦት እንደሚውልም ድርጅቱ አስታውቋል፡፡

የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ያደረገችው ድጋፍ በትክክለኛው ሰዓት የተደረገ መሆኑን ገልጸው፤ በተቻለ ፍጥነት ድጋፍ እንዲደርስ የሚደረግ መሆኑን ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም